ቻይንኛን በቶሎ - 0924894121

ክፍል አንድ : ቻይንኛ ቋንቋ መማር ከባድ ነው?

እንኳን ወደ Ethiotasks ገፅ ቻይንኛን ከዳኒ ጋር ለመማር በደህና መጡ ! የመጀመሪያውን ደረጃ አልፋቹ እዚህ መታቿል። ስለዚህ የቻይንኛ ቋንቋን መልመድ ትፈልጋላቹ ማለት ነው። ስለሆነም ቻይንኛ ቋንቋን የማትቹሉበት ምክንያት አይኖርም ፤ ይህ ጉጉት እስካላቹ ድረስ። ዛሬ ለመግቢያ እንዲሆን ቻይንኛ ምን ያህል ቀላል እንደሆነ እንመለከታለን።

Learn Chinese With Danny

7/12/20241 分钟阅读

1. ቻይንኛን መናገር

ቸ - ቹ - ቺ - ቻ - ቼ - ች - ቾ
እነዚህ 7 የአማርኛ ፊደላት ሲሆኑ ፤ ከእነዚህ መካከል 6ቱ የቻይንኛ ቃላት ናቸው ''ቼ'' ብቻ ሲቀር። ስለዚህ የቻይንኛ ቃላትን መናገር ለኢትዮጲያውያን ከባድ አይደለም።

2. ቻይንኛን መስማት

ብዙ የቻይንኛ ድምፆች በአማርኛ ትርጉም ስለሚሰጡን ለመስማት አይከብድም። ለምሳሌ :-
በአማርኛ ''ላይ'' የሚባለው ቃል። በቻይንኛ ''ና'' የሚል ትርጉም አለው።

3. ቻይንኛ ማንበብ

ይህም በጣም ቀላል ሲሆን ፤ ከአማርኛ ፅሁፍ ጋር ይቀራረባል። ለምሳሌ :-
''ተ'' የሚለው የአማርኛ ፊደል በቻይንኛ አስር ቁጥርን ያመለክታል።

4. ቻይንኛ መፃፍ

ቻይንኛ ፅሁፍ በጣም አዝናኝ ነው ፤ ለመልመድም ቀላል። ለምሳሌ በሮማን ቁጥር ከአንድ እስከ ሶስት ፃፋቹ ማለት በተዘዋዋሪ በቻይንኛ ከአንድ እስከ ሶስት ፃፋቹ ማለት ነው።
ምሳሌ : -
በቻይንኛ 1 ቁጥር ሲፃፍ ''一'' ነው !
በቻይንኛ 2 ቁጥር ሲፃፍ ''二'' ነው !
በቻይንኛ 3 ቁጥር ሲፃፍ ''三'' ነው !

    ጥያቄ ( Quize )  ይሞክሩ !